iLove Stories

A Free Portal for Read online Stories

Latest

Wednesday 22 April 2020

5+ top Stories Amharic Language


 * ምድርና በእርስዋ ውስጥ ያሉ ነገሮች ከመፈጠራቸው በፊት እግዚአብሔር ነበር። * በመጀመሪያው ቀን እግዚአብሔር “ብርሃን ይሁን አለ።” ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው። ጨለማውን ደግሞ ሌሊት ብሎ ጠራው። * በሁለተኛው ቀን እግዚአብሔር ሰማይን ሰራ። * በሶስተኛው ቀን እግዚአብሔር የብስን (ምድርን) ከውኆች ለየ። እንዲሁም አበቦችን፣ ዛፎችንና ሳርን ፈጠረ። *. በአራተኛው ቀን እግዚአብሔር ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ፈጠረ። * በአምስተኛው ቀን የሰማይ አእዋፍና በውኃ ውስጥ የሚዋኙ አሳዎችን ፈጠረ። * በስድስተኛው ቀን እግዚአብሔር እንስሳትን ፈጠረ። እንዲሁም እርሱን የሚመስሉ ሰዎችን ፈጠረ። እግዚአብሔር ወንዱን አዳም ብሎ ሲጠራው አዳም ደግሞ ሚስቱን ሔዋን ብሎ ጠራት። * በሰባተኛው ቀን እግዚአብሔር አረፈ። የፈጠረውን ነገር ሁሉ ተመልክቶም ሁሉ መልካም እንደሆ አየ። * ለሰራቸው ወንድና ሴት ሰዎች እግዚአብሔር መኖሪያ ይሆናቸው ዘንድ ኤደን ገነትን እግዚአብሔርም በገነት ከሚገኙት ዛፎች ሁሉ ፍሬ መብላት እንደሚችሉ ነገራቸው። ሆኖም ክፉንና መልካምን ከሚያስለየው ዛፍ ፍሬ እንዳይበሉ። አዘዛቸው። ሆኖም እባብ የሚባለው ፍጥረት ሔዋንን አታለላትና እንዳይበሉ ከታዘዙት የዛፍ ፍሬ በላች። ለአዳምም ከዚህ የዛፍ ፍሬ ሰጠችውና በላ። እግዚአብሔርን ስላልታዘዙት ከሚያምረው ቤታቸው ተባረሩ። ከዚህ በኋላም ከባድ ስራ መስራት ጀመሩ። ብዙ ችግርም ገጠማቸው። * እግዚአብሔር የሚለውን መስማት ሁሌም ጠቃሚ ነው። የፍጥረት ታሪክ የሚገኘው በመፅሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት መፅሐፍ በምዕራፍ 1፣ 2 እና 3 ነው።





 * ኖህ እግዚአብሔርን የሚታዘዝ መልካም ሰው ነበር። እርሱ በነበረበት ዘመን የነበሩ ሌሌች ሰዎች ግን ክፉዎች ነበሩ። * እግዚአብሔር ኖህን የጥፋት ውኃ ልኮ ምድርን እንደሚያጠፋት ነገረው። ስለዚህ ትልቅ መርከብ እንዲሰራ አዘዘው። * እግዚአብሔር ከሁሉም የእንስሳትና የአእዋፍ አይነቶች ሁለት ሁለት አድርጎ ወደኖህ ላካቸው። ኖህም ወደመርከቡ አስገባቸው። አንዳንድ የእንስሳት ዝርያዎች ከሁለት በላይ ሆነው ወደ ኖህ መርከብ ገቡ። ኖህ በተጨማሪም ሶስት ልጆቹና ሶስት ሚስቶቻቸውን እንዲሁም የራሱን ሚስት ይዞ መርከብ ውስጥ ገባ። ዝናብ መዝነብም ጀመረ። እግዚአብሔርም የመርከቡን በር ከውጭ በኩል ዘጋው። * ዝናቡም ያለማቋረጥ ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት ዘነበ። በምድር ላይ የነበሩ ማናቸውም ነገር ከውኃ በታች ሆኑ። በምድር የቀሩ ሰዎች በሙሉ ሞቱ። ኖህና ቤተሰቡ ግን ከጥፋት ውኃ አመለጡ። * ዝናቡ ካቆመ በኋላና ምድሩ ከደረቀ በኋላ እግዚአብሔር ቀስተደመናን በሰማይ ላይ በማድረግ ዳግመኛ ምድርን በጥፋት ውኃ እንደማያጠፋት ቃል ኪዳን አደረገ። የኖህና የጥፋት ውኃ ታሪክ የሚገኘው በብሉይ ኪዳን በዘፍጥረት መፅሐፍ በምዕራፍ 6፣7፣8 እና 9 ከቁጥር 1 – 17 ነው።




 አንድ ቀን እግዚአብሔር አብራምን ወደአዲስ ምድር እንዲሄድ አዘዘው። ሚስቱን ሳራይንና የአጎቱን ልጅ ሎጥን ይዞ ወደ ከነአን ምድር ሄደ።  አብራምና ሎጥ ሁለቱም ሀብታሞችና ብዙ የከብት መንጋዎች ነበሯቸው። እንስሶቻቸውን ይጠብቁ የነበሩ እረኞቻቸው እርስ በርስ ስለተጣሉ የነበሯቸውን መንጎች ለመከፋፈልና ለመለያየት ወሰኑ። አብርሃም የመጀመሪያውን ምርጫ ለሎጥ ተወለት። ሎጥም ምርጥ የሆነውን አካባቢ መርጦ ወደዚያው ሄደ። አብርሃም ደግሞ ከሎጥ ምርጫ የተረፈውን አካባቢ ወሰደ።  እግዚአብሔርም የአብራምን ስም አብርሃም ብሎ ቀየረለት። እግዚአብሔር በተጨማሪም አብርሃምን እንደሚባርከውና ትልቅ ቤተሰብ እንደሚሰጠው ቃል ገባለት።  አንድ ቀን ሶስት ሰዎች አብርሃም ሊጎበኙት መጡ። ሳራ በቅርብ ጊዜ እንደምትወልድ ነገሩት። በዚያን ጊዜ ሳራ እድሜዋ 90 ዓመት ሲሆን አብርሃም ደግሞ የ100 ዓመት የዕደሜ ባለጠጋ ነበር።  ይስሐቅም ልክ ሶሰቱ ሰዎች እንደተናገሩት ተወለደ። አንድ ቀን እግዚአብሔር አብርሃም ይስሐቅን እንዲሰዋ አዘዘው። እግዚአብሔር የእውነት ይስሐቅን እንዲሰዋው አስቦ ሳይሆን እምነቱን ሊፈትነው ፈልጎ ነበር ይህን ያለው። አንድ መልአክም የይስሐቅን ሕይወት አዳነ። የአብርሃም ታሪክ በዘፍጥረት ምዕራፍ 13፣18፣21 እና 22 ውስጥ ይገኛል።





 ያዕቆብና ኤሳው መንትያዎች ነበሩ። ሆኖም ኤሳው የበኩር ልጅ ነበር። የበኩር ልጅ እንደመሆኑ መጠን ደግሞ ከወንድሙ ጋር ከሚወርሱት ከአባታቸው ርስት በርከት ያለውን የመውረስ መብት አለው።  ያዕቆብ ብዙ ጊዜውን የሚያሳልፈው በወላጆቹ ድንኳን አካባቢ አንዳንድ ስራዎችን እየሰራ ነበር። ኤሳው ግን አዳኝ ነበር። ያዕቆብ ለስላሳ ገላ ሲኖረው ኤሳው ግን መላ ሰውነቱ በፀጉር የተሸፈነ ነበር።  አንድ ቀን ያዕቆብ ወንድሙን ኤሳውን በማታለል የብኩርናመብቱን ወሰደበት። ይህንንም ያደረገው ኤሳው በጣም በተራበበት ሰዓት ነበር። ታዲያ በጣም የተራበው ኤሳው ወንድሙን ያዕቆብን ሲያበስለው ከነበረው ምግብ እንዲሰጠው ይጠይቀዋል። ያዕቆብ ግን ኤሳው ብኩርናውን ሊሸጥለት ካልተስማማ እንደማይሰጠው ይነግረዋል። በዚህ መንገድ ያዕቆብ የኤሳውን ብኩርና ወሰደበት።  ከዚያም አንድ ቀን ይስሓቅ ልጁን ኤሳውን ሊባርከው ፈልጎ በመጀመሪያ አድኖ ከሚያመጣቸው እንስሳት የሚወደውን ምግብ እንዲያዘጋጅለት ይጠይቀዋል። ታዲያ ይህን የሰማችው እናታቸው አባትዬው የሚፈልገውን ምግብ ታዘጋጅና ለያዕቆብ ትሰጠዋለች። በእጁና በአንገቱ ላይም የፍየል ቆዳ ታለብሰዋለች። በተጨማሪም ከኤሳው ልብሶች መካከል ትመርጥና ያዕቆብን ታለብሰዋለች። ይህም ወደ አባቱ ይስሓቅ ለምርቃት ሲቀርብ ኤሳውን ለመምሰልና አባቱን ለማታለል እንዲረዳው ነው። ይህም ተንኮላቸው ሰራ። ያዕቆብ አባቱን አታሎ የወንደሙን ምርቃት ተቀበለ።  ኤሳው ከአደን ተመልሶ ይህን የወንደሙን ድርጊት በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ። ስለዚህ ያዕቆብ የነበረው ምርጫ መሸሽ ብቻ ነበር። አለበለዚያ ወንድሙ ኤሳው እጅግ ስለተበሳጨ ይገድለዋል። ያእቆብም በመሸ ጊዜም ድንጋይ ተንተርሶ ተኛ።  ሕልምንም አለመ። ባየው ሕልምም መሰላል ከምድር እስከሰማይ ድረስ ተዘርግቶ መላእክት በመሰላሉ ወደላይና ወደታች ሲወርዱና ሲወጡ ተመለከተ። ከመሰላሉ ጫፍ ላይ እግዚአብሔር ነበረበት። እግዚአብሔርም  ያዕቆብን ከክፉ ሁሉ እንደሚጠብቀውና ትልቅ ቤተሰብ እንደሚሰጠው፣ እንዲሁም አሁን ያረፈበትን ምድር እንደሚያወርሰው ቃል ገባለት።  ከእንቅልፉ ሲነቃም ለእግዚአብሔር ሰገደ። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነም ከሚያገኘው ከማናቸውም ነገር አንድ አስረኛውን ለእግዚአብሔር ለመስጠት ቃል ገባ።  ከዚህ በኋላም ያዕቆብ ሚስቶችን አግብቶ አስራ ሁለት ልጆችን ወለደ። ስሙም እስራኤል ተባለ። ቤተሰቦቹም አስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ተብለው መጠራት ጀመሩ። የያዕቆብና የኤሳው ታሪክ በመፅሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት መፅሓፍ ከምዕራፍ 25 እስከ ምዕራፍ 27 ድረስ ይገኛል።




* ዮሴፍ በምድረ ግብፅ አገረ ገዢ ሆነ። በሥልጣን የመጀመሪያው ሰው ፈርኦን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ዮሴፍነበር። ዮሴፍ ግብፃዊት ሚስት ተሰጠው ሁለት ልጆችንም ወለደችለት።*ጥሩ ምርት በነበረባቸው 7 ዓመታት ዮሴፍ ሕዝቡ እህል እንዲያከማቹ አደረጋቸው። ከሰባቱ አመታት በኋላዝናብ አቆመ የእህል ምርትም ቆመ። በምድር ላይ ድርቁ እጅግ የበረታ ሆነ። በዚያን ጊዜ እህል የሚገኝባት አገርግብፅ ብቻ ነበረች።* ያዕቆብ እህል ይገዙ ዘንድ አስሩን ልጆቹን ወደ ግብፅ ላካቸው። ወንድማማቾቹ ለዮሴፍ ዝቅ ብለውበግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱለት። ዮሴፍ ወንድሞቹ እንደሆኑ አወቀ። እነርሱ ግን አላወቁትም። ምግብሰጣቸው። ከእነርሱ አንደኛውን በወህኒ ቤት አኖረው። እንደገና ወደ ግብፅ ምድር ለእህል ሸመታ ሲመለሱ ታናሽወንድማቸውን ይዘው እንዲመጡ አዘዛቸው። ( ቢንያም የዮሴፍ ታናሽ ወንድሙ ነው።)* ያዕቆብ ቢንያምን ለመላክ ፈራ። ሆኖም ወንድሞቹ እህል ለመሸመት ወደ ግብፅ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሄዱቢንያምን ይዘውት ሄዱ። በዚህ ጊዜ ግን ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን ገለጠላቸው። ከዚህ በፊት በእርሱ ላይከፈፀሙት ክፋት የተነሳ ይበቀለናል ብለው ሰጉ። ዮሴፍ ግን ይቅር ባይ ነበር። በምድር ላይ የተከሰተው ድርቅ ገናረዘም ላለ ጊዜ ስለሚቆይ ወደ ከነአን ምድር ተመልሰው አባታቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ይዘው እንዲመጡነገራቸው።* ስለ ዮሴፍ በሕይወት መኖር በሰማ ጊዜ ያዕቆብ እጅግ ደስ አለው። ያዕቆብና መላ ቤተሰቡ ወደ ግብፅ ወረዱ።ያዕቆብም እንደገና ማየት ቻለ።* ድርቁ ለሰባት አመታት ቆየ። ግብፃውያን ያላቸው እህልና ገንዘብ አለቀባቸው። ስለዚህ ከብቶቻቸውንናእንስሶቻቸውን በእህል ለወጡ። ከዚህ የተነሳም ግብፃውያን በሙሉ የፈርኦን አገልጋዮች ሆኑ። ዮሴፍና ቤተሰቦቹግን ብዙ እህል ባለበት በጌሴም ምድር ተቀመጡ። የዮሴፍና የወንድሞቹ ታሪክ የሚገኘው በዘፍጥረት 42፣43፣44፣45፣46፣ እና 47 ነው።

No comments:

Post a Comment